About Us
መነሻ ሀሳብ
ለምን ደኃ ሆነን ?
ረጅሙን ታሪክ በአጭሩ ለመናገር ያህል ለኢትዮጵያ ሕዝብ ድህነት መንስኤዎች ስንፍና፤ ድንቁርና፤ ልመና፤ሙስና ፤ ምስፍና እና አፈና ናቸው ። እነዚህ ስድስት የድህነት መንስኤዎች አሥር የድህነት መገለጫዎችን ያንጸባርቃሉ። የሥራና የትምህርት እጦትን፤ የጦርነትና የግጭት ችግሮችን፤ የአየር ንብረት መዛባትን፤ ማህበራዊ ኢ-ፍትሓዊነትን፤ የምግብና የውኃ እጥረትን፤ የመሠረተ-ልማትና የመንግስት ድጋፍ ጉድለትን፤ የጤና እንክብክቤ አለመኖርን፤ የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነትን ያስከትላሉ። ለእነዚህ እጥረቶችና እጦቶች መጋለጥ አስከፊ ድህነት ውስጥ መውደቅን ያረጋግጣል።
ስለዚህ ያደጉ አገሮች ከስንፍና ይልቅ ትጋትን፤ ከድንቁርና ይልቅ ዕውቀትን ፤ ከልመና ይልቅ ሰርቶ ማግኘትን፤ ከሙስና ይልቅ ታማኝነትን፤ ከምስፍና ይልቅ ዴሞክረሲን፤ ከአፈና ይልቅ የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ለማደግ ችለዋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብም ይህንን ለማድረግ መወሰን አለበት። እንደ ሕዝብ በመሰባሰብና በመደራጀት የራሱን ዊዝደም በመጠቀም፤ በተፈጥሮ ጸጋው በመገልገል፤ ከድህነት መውጣት አለበት። ሌላ ሰው መጥቶ ከድህነት ጎትቶ እንዲያወጣው መጠበቅ የለበትም። እራሱን በራሱ ከችጋር ማላቀቅ አለበት። የኒኦ ሶሳይቲ መነሻ ሃሳብ ይኼው ነው። በራሳችን ለራሳችን ከድህነት አዘቅት መውጣት!!ምክንያቱም የሁሉም ችግሮቻችን ምንጭ ድህነት ስለሆነ።
Latest News
April 10, 2023 Published a new event.